የሰላም እጦቱ ወጣቶችን ሥራ ፈትተው ለመጤ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት እንዲጋለጡ ማድረጉን የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ገለጸ፡፡

11

ባሕር ዳር: ታኅሳስ 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከክልሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር “የወጣቶች ጉዳይ ትግበራ አሉታዊ መጤ ባሕል እና አደንዛዥ ዕጾች መከላከል ግብረ ኃይል የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ” በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኀላፊ እርዚቅ ኢሣ የአማራ ክልል በሰሜኑ ጦርነት ከደረሰበት ሰብዓዊ፣ ሥነ ልቦናዊ እና ቁሳዊ ጥቃት ብሎም ውድመት ሳያገግም ለሌላ የሰላም እጦት መዳረጉ በርካታ ወጣቶችን ለድብርት እንዲዳረጉ ማድረጉን ገልጸዋል።

እንደ ኀላፊው ገለጻ የሰላም እጦቱ በርካታ ወጣቶችን ሥራ ፈትተው ለመጤ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት እንዲጋለጡ አድርጓል። ወጣቱን ካለበት ችግር አስወጥቶ በንቃት ወደ ሥራ ለማሰማራት የማያሳስበው ሰውና ተቋም የለም ብለዋል። ተቋማት በአካቶ ትግበራ ወጣቱ ላይ ሲሠሩ ብቻ ነው የወጣቱን ሕይወት መታደግ የሚቻለው ነው ያሉት አቶ እርዚቅ።

ዘጋቢ፡- ሙሉጌታ ሙጨ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየተፈጠረው የጸጥታ ችግር በጤና ሥራዎች ላይ እንቅፋት እየፈጠረ መኾኑን የአማራ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ።
Next article“የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝን ጨምሮ 40 በሚኾኑ ዘር አባዥ ድርጅቶች የተባዛ ምርጥ ዘር እየተሰበሰበ ነው” የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ