
ባሕርዳር: ታኅሳሥ 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከሊግ ካንፓኒ፣ ከከተማው የስፖርት ክለብ ደጋፊዎች፣ ከብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች እና ከመላው የስፖርት ቤተሰቦች ጋር በስፖርታዊ ጨዋነት ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል።
የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ስፖርቱን የማይወክሉ አንዳንድ ደጋፊዎች በስታዲየም ውስጥ የሚፈጥሩትን ሁከት በጋራ መከላከል ይገባል።
በሁሉም የስፖርት ዘርፍ በጋራ በመሥራት ለሁለንተናዊ የስፖርት እድገትና ልማት መረባረብ እንደሚገባ ገልጸዋል። ስፖርቱን የማይወክሉ አካላት የጨዋታ ሜዳዎችን የሁከትና ብጥብጥ ማዕከል ለማድረግ የሚያደርጉትን ጥረት መከላከል እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ለስፖርታዊ ጨዋነት እድገት እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ የእግርኳስ ደጋፊዎችም እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በውይይት መድረኩ የተገኙት የተለያዩ ክለብ ደጋፊዎችና የስፖርቱ ቤተሰቦች ስፖርታዊ ጨዋነት አስፈላጊ መኾኑን ጠቅሰዋል። እግር ኳስ የሰላም ምንጭ እንጂ የግጭት ምክንያት ሊሆን አይገባም ብለዋል፡፡
በተጨማሪም ስፖርታዊ ጨዋነትን በመጣስ ያልተገባ ሁከት የሚፍጥሩ ደጋፊዎችን በመነጥል ተጠያቂ ማድረግ እንደሚገባ መናገራቸውን ከቢሮው የተገኘ መረጃ ያስረዳል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!