የመውሊድ በዓል አከባበር ሥነ-ሥርዓትን በዩኔስኮ የማይዳሰስ ቅርስነት ለማስመዝገብ ያለመ ውይይት ተካሄደ።

36

ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመውሊድ በዓል አከባበር ሥነ-ሥርዓትን በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) በማይዳሰስ ቅርስነት ለማስመዝገብ ያለመ የጥናት ማስጀመሪያ ውይይት አካሄደ፡፡

ዩኒቨርሲቲው በእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ በየዓመቱ በድምቀት የሚከበረውን የመውሊድ በዓል ባሕላዊ መልኮችን በማጥናት ለማሳየት ያለመ መኾኑ ተገልጿል፡፡

በመድረኩ ሦስት ጥናታዊ ጹሑፎች ቀርበው ውይይት የተካሄደባቸው ሲኾን፤ የእምነቱ ተከታዮች እና መምህራንን ጨምሮ በርካታ አካላት በውይይቱ ተሳትፈዋል።

ፋብኮ እንደዘገበው፤ የጥናት ማስጀመሪያ መርሐ ግብሩን ያዘጋጀው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ባሕል አካዳሚ ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጣራ ገዳም – የሃይማኖታዊ ታሪክ ባለቤት፣ የሀገር በቀል ዛፎችም ባንክ
Next article“በየዓመቱ ከ130 ሺህ ኩንታል በላይ ቡና እናመርታለን፤ ወደ ውጪም መላክ ጀምረናል” የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ