
ባሕር ዳር: ታኅሳስ 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የአማራ ክልል ኢንደስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኀላፊ እና የፍትሕ ተቋማት መምሪያ ኀላፊዎች በደብረ ብርሃን ከተማ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችን ጉብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱ የክልሉ ኢንደስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኀላፊ እንድሪስ አብዱ በደብረ ብርሃን ከተማ የሚገኙ ኢንደስትሪዎችን ወቅታዊ ሁኔታውን ተቋቁመው እየሠሩ መኾናቸው የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡
ነዋሪዎች ሰላማቸውን ለማስጠበቅ ያላቸው ቁርጠኝነት የሚደነቅ ነው ያሉት ቢሮ ኀላፊው “የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪ ሃብቱን አክብሮ በመያዙ የኢንደስትሪ ፍሰቱ እየጨመረ መጥቷል”
ቢሮው በዛሬው ዕለት በኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ዙሪያ በወጡ አዳዲስ ሕጎች፣ አሠራሮች እና ደንቦች ላይ ከፍትሕ አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል።ብለዋል።
ዘጋቢ፡- እስከዳር ገበየሁ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!