የቡና አምራች አርሶ አደሮች የመስክ ትምህርት የአሠልጣኞች ሥልጠና በባሕር ዳር ተጀመረ።

19

ባሕር ዳር: ታኅሳሥ 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የቡና እና ሻይ ባለሥልጣን በኢዩ-ካፌ ፕሮጀክት የሚደገፍ የቡና አምራች አርሶ አደሮች የመስክ ትምህርት የአሠልጣኞች ሥልጠና በባሕር ዳር ተጀምሯል።

በሥልጠናው ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኀላፊ ቃልኪዳን ሽፈራው አማራ ክልል ለቡና ልማት ምቹ የኾነ የእርሻ ምህዳር ያለው መኾኑን ገልጸዋል። አካባቢውን በአግባቡ ከተጠቀምንበት ክልሉ የተሻለ የቡና ምርት የሚመረትበት ይኾናል ብለዋል፡፡

የቡና ልማቱን ውጤታማ ለማድረግ ኢዩ-ካፌ እያገዘ መኾኑን ጠቅሰው ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል። የኢፌዴሪ ቡና እና ሻይ ባለሥልጣን በአማራ ክልል ያለውን ምቹ ሁኔታ በማየት ልማቱን እንዲደግፍ እና እንዲያበረታታም አቶ ቃልኪዳን ጠይቀዋል።

ዘጋቢ፡- ዋሴ ባየ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየገና እና የጥምቀት በዓላትን በደመቀ ሁኔታ ለማክበር በቂ ዝግጅት እየተደረገ መኾኑን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ።
Next articleየዋንጫ ተፎካካሪነትን ለማጠናከር እና ከወራጅ ቀጣና ለመራቅ ኤቨርተን ከማንቸስተር ሲቲ የሚደረግ ትንቅንቅ፡፡