
ባሕር ዳር: ታኅሳሥ 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ አምና ከሠራነው በብዙ ይበልጣል ብለዋል። በዘርፉ እስካሁን የተገኘው ውጤትም እጅግ አመርቂ ነው ሲሉም ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሰፈሩት “በአመት ከአንዴ በላይ በማረስ የምግብ ሉአላዊነታችንን አስተማማኝ በሆነ መልኩ ለማረጋገጥ የምናረገው ጥረት እየተሳካ ነው” ብለዋል። በሁሉም መስክ የሚደረገው ጥረት የብልጽግና መሰረት ይጥላል ሲሉም ተናግረዋል ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!