
ባሕር ዳር: ታኅሳሥ 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የበዓል ሰሞን/የቦክሲንግ ደይ/ በአጭር ቀናት ውስጥ ተደራራቢ ጨዋታዎች ይከወኑበታል።
ዛሬ ከሚከናወኑ ጨዋታዎች መካከል በውጤት ማጣት እየተፈተነ ያለው ማንቸስተር ዩናይትድ የዘንድሮውን ጠንካራ ቡድን አስቶን ቪላን የሚገጥምበት ጨዋታ ይጠበቃል። በዩናይትድ በኩል አሁን የክለቡ ወሳኝ ተጫዋቾች ጉዳት ላይ ስለመኾናቸው ክለቡ በይፋዊ ገጹ አስታውቋል። ጨዋታው ምሽት 5 ሰዓት ይካሄዳል።
በቀሪ ጨዋታዎች በርንማውዝ ከፉልሃም፣ ሼፊልድ ከሉተን ምሽት 12 ሰዓት ይጫወታሉ። በርንለይ እና ሊቨርፑል ምሽት 2:30 ይገናኛሉ። የ19ኛ ሳምንት ቀሪ ጨዋታዎች ረቡዕ እና ሐሙስ ይከናወናሉ።
የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግን አርሰናል በ40 ነጥብ ይመራዋል።ሊቨርፑልና አስቶን ቪላ በእኩል 39 ነጥብ በግብ ተበላልጠው ቀጣዮችን ደረጃዎች ይዘዋል። አዲስ አዳጊዎቹ ሉተን፣ በርንለይ እና ሼፊልድ የመጨረሻዎቹ ሦስት ደረጃዎች ላይ ተቀምጠዋል።
በአስማማው አማረ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!