“በመንግሥት በኩል የሚሰጠንን ተልዕኮ ለመፈጸም ዝግጁ ነን” የቀድሞ የአማራ ልዩ ኀይል አባላት

19
RemasterDirector_1a5c03258

ባሕር ዳር: ታኅሳሥ 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በጎንደር ዙሪያ ወረዳ የቀድሞው የአማራ ልዩ ኀይል አባላት በመንግሥት በኩል የሚሰጣቸውን ተልዕኮ ለመፈጸም ዝግጁ መኾናቸውን ተናግረዋል።

በወረዳው የሚገኙ የቀድሞው የአማራ ልዩ ኀይል አባላት ከመንግሥት ጋር ለመሥራት የሚያስችል ውይይት ከወረዳው አሥተዳደር ጋር አድርገዋል።

በውይይቱ ከ108 በላይ የሚኾኑ የቀድሞው የአማራ ልዩ ሀይል አባላት ተሳትፈዋል። በመንግሥት በኩል የሚሰጣቸውን ተልእኮ ለመፈጸም ዝግጁ መኾናቸውንም ተናግረዋል።

የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ ኤርሚያስ ቢራራ በወረዳው የሚገኙ የቀድሞውን የአማራ ልዩ ኀይል አባላትን ተቀብለው አወያይተዋል። ይህን የሠለጠነ ኀይል በአስተሳሰብ በማነፅ በቀጣይ ሀገርን ሊገነባ የሚችል ለማድረግ እንሠራለን ማለታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየምን የሥራ እንቅሥቃሴ ተመለከቱ።
Next articleየበዓል ሰሞን የእንግሊዝ ፕሪሜየር ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ ይጀመራሉ።