የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም 52 ሺህ ዘመናዊ ወንበር ሊገጠምለት እንደኾነ የአማራ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ገለጸ፡፡

13

ባሕር ዳር: ታኅሳሥ 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም 52 ሺህ ዘመናዊ ወንበር ለመግጠም ተቋራጩ ተለይቶ ወደ ሥራ መገባቱን የአማራ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኀላፊ እርዚቅ ኢሳ ገልጸዋል፡፡

ቢሮ ኀላፊው እንደገለጹት የወንበር ገጠማ ሥራውን የሚያከናውነው በሜድሮክ-ኢትዮጵያ ሥር ያለ “አዲስ ጋዝ” የተሰኘ ንዑስ ተቋራጭ ነው፡፡ ለወንበር ገጠማው የሚያገለግሉ ልዩ ልዩ ዕቃዎች ከቻይና መምጣታቸውንም አስረድተዋል፡፡

ቢሮ ኀላፊው የሚገጠመው ወንበር የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) እና የዓለም አቀፉን እግር ኳስ ማኀበር (ፊፋ) የደረጃ መስፈርትን ያሟላ ነውም ብለዋል፡፡ ለስታዲየሙ የሚገጠመው ወንበር ዘመናዊ መኾኑንም ነው ቢሮ ኀላፊ የገለጹት፡፡

የአማራ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሠራተኞች “ከዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ መልዕክት የተሰጣቸውን ሥልጠና ካጠናቀቁ በኋላ የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየምን የግንባታ ሂደት ጎብኝተዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ሙሉጌታ ሙጨ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleMaxxansa Gaazexaa Hirkoo: Mudde15/2016
Next article“የኃይል አቅርቦት ችግሩን ለመፍታት የክልሉ መንግሥት ትኩረት ሠጥቶ ይሠራል” የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን