
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ፣ የብሔራዊ መረጃ ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄኔራል ተመስገን ጥሩነህ፣ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች በባሕር ዳር የመሠረተ ልማት ሥራዎችን ተመልክተዋል።
ርእሰ መሥተዳድሩ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ከተመለከቷቸው ሥራዎች መካከል አዲሱ የዓባይ ድልድይ አንደኛው ነው።
ርእሰ መሥተዳድሩ በምልከታቸው “የመሠረተ ልማት ሥራዎች በፍጥነት መሠራት አለባቸው” ብለዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!