
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አፈፃፀም ላይ የተደረገ የመስክ ምልከታ ሪፖርት በዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ቀርቧል።
ሪፖርቱ አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሚዲያ ተቋማት መሪዎች እና የምክክር ኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች በተገኙበት ቀርቧል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ በዚሁ ወቅት፤ በሀገራዊ ምክክሩ ትኩረት የሚሹ ዋና ዋና ጉዳዮችን በመለየት በተፈለገው ጊዜ እንዲጠናቀቅ ባለድርሻ አካላት ርብርብ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል።
ቋሚ ኮሚቴው በሲዳማ፣ በሐረሪ እና በቤንሻጉል ክልሎች እንዲሁም በኮሚሽኑ ዋና መ/ቤት በመገኘት የምክክር ኮሚሽኑ ተግባር እና ሂደት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ምልከታ ማድረጉ በቀረበው ሪፖርት ተመላክቷል።
በቀረበው ሪፖርት መነሻነትም ውይይት እየተደረገ መሆኑን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!