ምርቱ የላቀ የሆርቲካልቸር ሥራ ለማከናወን የተደረገው ጥረት አስደናቂ ውጤቶችን በማሳየት ላይ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ገለጹ።

25

ባሕር ዳር: ታኅስሥ 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በመስኖ የተደገፈ እና ምርቱ የላቀ የሆርቲካልቸር ሥራ ለማከናወን የተደረገው ጥረት አስደናቂ ውጤቶችን በማሳየት ላይ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሰፈሩት የአሥር ዓመቱ የልማት ዕቅድ ለፍራፍሬ ምርት እና ሌሎች አይነተኛ የዘርፉ ምርቶችን የሚያካትተውን የሆርቲካልቸር ልማት ሥራን ለማስፋፋት ያለመ ነው፡፡ በተለይም በፓፓያ ምርት ላይ የታየው ምርታማነት ዘርፉ አስደናቂ ውጤት እያመጣ ለመኾኑ አይነተኛ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበክልሉ ለሙቀት አማቂ ጋዝ ልቀት አስተዋጽኦ እያደረጉ የሚገኙ ተቋማትን ማዘመን እንደሚገባ ተገለጸ።
Next article“የሰላም እጦት ችግሩ የዘላቂ ህልውናችን መሰረት በኾነው ጣና ሐይቅ ላይም የከፋ ፈተና ደቅኖበታል” የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ