
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የ71 ዓመቱ ጂም ኦልድትራፎርድ ስታዲየምን 300 ሚሊዮን ዶላር ለማደስም ነው የተስማሙት ተብሏል።
የማንቸስተር ከተማ ተወላጅ የኾኑት ራትክሊፍ የፔትሮ ኬሚካልስ ኩባንያ እና የኢኔኦስ ስፖርት ሊቀመንበር ሲኾኑ “የማንቸስተር ዩናይትድ የዕድሜ ልክ ደጋፊ” እንደኾኑም ተናግረዋል። ባለሀብቱ ባለፈው ዓመት ቼልሲን ለመግዛት ሞክረው እንዳልተሳካላቸው ቢቢሲ በድረ ገጹ አስነብቧል፡፡
ቢሊየነር ሰር ጂም ራትክሊፍ እንዳሉት “በክለቡ ውስጥ ተጨማሪ መሻሻልን ለማምጣት ኦልድትራፎርድን ማደስ ግድ ነው፡፡ ለዚህም 300 ሚሊዮን ዶላር ለማፍሰስ ማቀዳቸውንም ተናግረዋል፡፡
“ተጋግዘን ክለቡ ላይ ከሠራን ማንቸስተር ዩናይትድን ወደ ገናናነት መመለስ እንችላለን ፤ እኔም እውቀቴንና ገንዘቤን በማፍሰስ ክለቡ በዓለም እግር ኳስ አናት ላይ እንዲቀመጥ ምኞቴን በተግባር ለማየት ጓጉቻለሁ”ብለዋል- ሰር ጂም ራትክሊፍ ።
ራትክሊፍ የኢንኦስ ኬሚካሎች ኩባንያ የኬሚካል መሐንዲስ እና ነጋዴ ናቸው ፡፡ በ2021 ኩባንያቸው የ65 ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንዳገኘም ይገመታል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!