“ኢትዮጵያ ጸጋዎቿን በመጠቀም ለቀጣዩ ትውልድ እዳን ሳይኾን ምንዳን ለማስተላለፍ አባላት፤ ሌት ከቀን ለመሥራት የጋራ አቋም የሚወስዱበት ነው” የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት

15

ባሕርዳር: ታኅሳሥ 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ለዞኑ የመንግሥት ሠራተኛ አባላት የአቅም ግንባታ ሥልጠና እየሰጠ ነው፡፡

”ከዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ መልዕክት 5ኛው ዙር የአቅም ግንባታ ሥልጠና ለመንግሥት ሠራተኛ አባላት በጎንደር ማዕከላት መስጠት ተጀምሯል፡፡

በሥልጠናው ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ፈንታሁን ስጦታው፣ በዚህ ስልጠና ከአንድ ሺህ እስከ ሁለት ሺህ የመንግስት ሠራተኛ አባላት እየተሳተፉ እንደኾነ ጠቅሰው፤ ከታኅሳሥ 15/2016 ጀምሮ ለ4 ተከታታይ ቀናት ይሰጣል ብለዋል።

የአቅም ግንባታ ስልጠናው በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በሀብት ፈጠራ፣ በገዥ ትርክትና በሰላም ግንባታ ዙሪያ አንደሚያተኩርም ገልጸዋል።አቶ ፈንታሁን ሥልጠናው የአባላትን አቅም በማሳደግ በኩል ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል።

በመኾኑም ሥልጠናው እጅግ አስፈላጊ በመኾኑ አባላት በተገቢው መንገድ ተከታትለው ተቀራራቢ እውቀትና ግንዛቤ እንዲጨብጡ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ከእዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ሐሳብ እየተሰጠ ባለው ሥልጠናም ኢትዮጵያ ጸጋዎቿን በመጠቀም ለቀጣዩ ትውልድ እዳን ሳይኾን ምንዳን ለማስተላለፍ አባሉ ሌት ከቀን መሥራት እንዳለበት የጋራ አቋም የሚወስድበት እንደኾነ ነው የገለፁት።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበደብረታቦር ከተማ የመንግሥት ሠራተኞችና የምሁራን አባላት የአቅም ግንባታ ሥልጠና መሰጠት ተጀመረ።
Next articleእንግሊዛዊው ቢሊየነር ሰር ጂም ራትክሊፍ የማንቸስተር ዩናይትድን 25 በመቶ ድርሻ በ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ለመግዛት መስማማታቸው ተነገረ።