“ትውልድ ላይ መሥራት ካስፈለገ ከሕጻናት ጤና ላይ በትኩረት መሥራት ይገባል” የአማራ ክልል ጤና ቢሮ

18

ባሕር ዳር: ታኅሳስ 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ዓለም አቀፍ ከመወለጃ ቀናቸው በፊት ለሚወለዱ ሕጻናት እና የሳንባ ምች በሽታ ወርን ምክንያት በማድረግ በባሕር ዳር ውይይት ተደርጓል።

የሳንባ ምች በሽታ ከአንድ ወር እስከ አምስት ዓመት እድሜ ላላቸው ሕጻናት ቀዳሚ የሞት መንስኤ እንደኾነ ይነገራል። የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኀላፊ አበበ ተምትሜ ያለ ቀናቸው የሚወለዱ ሕጻናት እና የሳንባ በሽታን ታሳቢ ያደረገ ቀን ማክበር የችግሩን አሳሳቢነት የሚያስረዳ መኾኑን ገልጸዋል። ከነገው ሀገር ተረካቢ ትውልድ ላይ መሥራት ይገባልም ብለዋል።

ሕጻናቱን መንከባከብ ትውልድን ማቆዬት መኾኑንም ተናግረዋል። የሳንባ በሽታን መከላከል እንደሚገባም ገልጸዋል። ካለቀናቸው የሚወለዱ ሕጻናት እና የሳንባ በሽታ የሕጻናትን ሞት ቁጥር እንደሚጨምረውም አንስተዋል።

ለጤናው ዘርፍ ትኩረት በመስጠት ጤናማ ትውልድ መፍጠር ግድ ይላልም ብለዋል። ካለ ቀናቸው ለሚወለዱ ሕጻናት እና የሳንባ በሽታ ችግሩ አሳሳቢ መኾኑንም በመገንዘብ መሥራት ይገባል ነው ያሉት። ከፅንስ ጀምሮ፣ በወሊድ እና ከወሊድ በኋላ እንክብካቤ ማድረግ እንደሚገባም አመላክተዋል። ያለ መወለጃ ቀናት የሚወለዱ ሕጻናት ቁጥር እየጨመረ መምጣቱም ተመላክቷል።

የሳንባ በሽታን በመከላከል እና በማከም የሕጻናት ሕይወትን መታደግ ይገባልም ብለዋል። ያለ እድሜያቸው የሚወለዱ ሕጻናት ሕይወታቸው ባያልፍ እንኳን ለዘላቂ ጤና ችግር ያጋልጣቸዋል ነው የተባለው። ሕፃናት ለሞት እንዳይዳረጉ እና ለበሽታ እንዳይጋለጡ በቂ እንክብካቤ ማድረግ ይገባል ነው ያሉት።

በእንክብካቤ ጉድለት ለበሽታ የሚጋለጡ ሕጻናት መኖራቸውንም ገልጸዋል። መፍትሔው ከራሳችን ጋር ነው ያሉት ምክትል ኀላፊው ለሕጻናት እንክብካቤ በመስጠት ትልቅ ውጤት ማምጣት እንደሚቻልም ተናግረዋል። የሳንባ በሽታ ለሕጻናት ሞት ቀዳሚው ነው ያሉት ምክትል ኀላፊው በመከላከል እና በማከም ሕይወታቸውን መታደግ እንደሚገባም ገልጸዋል።

የጨቅላ ሕጻናት ሞት በታቀደው ልክ እየቀነሰ አለመኾኑንም አመላከተዋል። በትኩረት እና በኀላፊነት በመሥራት የጨቅላ ሕጻናትን ሞት መቀነስ እንደሚገባም ገልጸዋል። ትውልድ ላይ መሥራት ካስፈለገ ከሕጻናት ጤና ላይ በትኩረት መሥራት ይገባል ነው ያሉት።

ዘጋቢ፦ ታርቆ ክንዴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“እየተካሄዱ ያሉ ሥልጠናዎች የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት እና የአመራሩን አቅም ለመገንባት እድል ይሰጣሉ” የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር
Next articleበአማራ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሚውል 11ሺህ ኩንታል የበቆሎ ዱቄት ወደ ሥፍራው እየተጓጓዘ መኾኑ ተገለጸ፡፡