
ደብረ ብርሃን: ታኅሳሥ 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ለአባላቱ ሥልጠና መስጠት ጀምሯል። የከተማ አሥተዳደሩ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሰለሞን ጌታቸው ዛሬ የተጀመረው ሥልጠና በሀገር አቀፍ ደረጃ “ከእዳ ወደ ምንዳ” በሚል ለአመራሩ ሲሰጥ የቆየው ሥልጠና አካል እንደኾነ ተናግረዋል።
በሥልጠናው አገልጋይ እና ሥልጡን የመንግሥት ሠራተኞችን መፍጠር የሚቻልበትን መንገድ ተነሰቶ ውይይት እንደሚደረግ ገልጸዋል።
የከተማ አሥተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት “እየተካሄዱ ያሉ ሥልጠናዎች የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት እና የአመራሩን አቅም ለመገንባት እድል ይሰጣሉ” ብለዋል። በሥልጠናው ላይ የተካተቱ ርዕሰ ጉዳዮች ሥራን በዕውቀት ለመምራት የሚያስችል እውቀት እና ክሕሎት የሚያስገኙ ስለመኾናቸውም ተናግረዋል።
ሠልጣኞችም ሥልጠናውን በሚገባ ተከታትለው ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት እንደሚያደርጉ ለአሚኮ ተናግረዋል።
ዘጋቢ፦ እስከዳር ገበየሁ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!