
ባሕር ዳር: ታኅሳሥ 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ባለፋት ሦስት ዓመታት የትምህርት ሥራ ውጣ ውረድ የበዛበት መኾኑ ይታወቃል። በክልሉ በርካታ ትምህርት ቤቶች በወረራ ምክንያት ወድመዋል፤ የመማሪያ ቁሳቁሶች ተዘርፈዋል፤ በተፈጠረው በጸጥታ ችግር ምክንያት ተረጋግቶ መማር ይቅር እና የፈተና ቀን እንኳን ሰክኖ ጥያቄን መጨረስ ለተማሪዎች አስቸጋሪ ኾኗል።
የአማራ ክልል በውጣ ውረድ ውስጥ ኾነውም ነገን የሚያዩ፣ ጫና ሳይበግራቸው በወርቅ ቀለም የሚጻፍ ታሪክን የሚሠሩ እና ባለብሩህ አዕምሮ ተማሪዎች አሉት።
በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ከፍተኛ ውጤት ላያስመዘገቡ ባለምጡቅ አዕምሮ ተማሪዎች የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሽልማት እና ዕውቅና እየሰጠ ነው።
በተበጋጀው የተማሪዎች የሽልማት እና ዕውቅና መርሐ ግብር ላይ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች እና የተማሪ ወላጆች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
