
ጎንደር: ታኅሳሥ 12/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በኅብረተሰቡ የሚነሱ የመልካም አሥተዳደር ጥያቄዎችን ለመፍታት እንደሚሠሩ በጎንደር ከተማ በሚሰጠው የብልጽግና ፓርቲ አባላት ሥልጠና የሚካፈሉ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተናግረዋል።
የሥልጠናው ተካፋዮች በቆይታቸው የሕዝብ ጥያቄዎችን መመለስ የሚያስችል ክህሎት ለማግኘት ሥልጠናው እንደሚያግዛቸውም ተጠቁሟል።
የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ቻላቸው ዳኘው የሥልጠናው ዋና አላማ በከተማ አሥተዳደሩ የሚነሱ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ችግሮችን ለይቶ ለመፍታት የሚያስችል አቅም ለመፍጠር ነው ብለዋል።
በሥልጠና መርሐ ግብሩ ገዢ ትርክት፣ ሀብት መፍጠርና መምራት፣ የሰላም ባሕልና አመለካከት የመፍጠርና የመገንባት ክህሎትና አገልጋይና ሥልጡን ሲቪል ሰርቪስ መገንባትና መምራት በሚሉ አጀንዳዎች ላይ እንደሚያተኩር ተገልጿል።
ዘጋቢ፦ ምስጋናው ከፍያለው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
