
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 12/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ. ር) “ከ2013 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ለ12ኛ ጊዜ ባካሄድኩት የኮይሻ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግምገማ በለወጥነው የፕሮጀክት አስተዳደር እና ክትትል ሥርዓት የተነሣ የአጠቃላይ ግንባታው ሂደት 62% ላይ መድረሱን በመመልከቴ ደስታ ተሰምቶኛል” ሲሉ ገለጹ።
“በአፍሪካ ደረጃ በግዙፍነታቸው አንደኛ እና ሦስተኛ የሆኑትን የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ እና የኮይሻ ግድቦች ባለቤት በመሆናችን የንፁህ የኃይል ማመንጨት ኃይችንን እና ጥረታችንን አቻ የሌለው ያደርገዋል” ሲሉም አክለዋል።
በቅርብ ርቀት በጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ የሚገኘውን የጨበራ የዝሆን ዳና ሎጅን በምንመርቅበት በአሁኑ ወቅት የኮይሻ ግድብ ለአካባቢው የቱሪዝም ዕድል ተጨማሪ አስተዋፅኦ ያደርጋል ሲሉ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አስታውቀዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!