
ባሕር ዳር: ታኅሳሥ 12/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የብልጽግና ፓርቲ አባላት አምስተኛው ዙር ሥልጠና በባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር በኹሉም ክፍለ ከተሞች ተጀምሯል። ሥልጠናው የአመለካከት እና የአስተሳሰብ አንድነት በሚያመጡ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ አተኩሮ መሰጠት እንደተጀመረ ሠልጣኞች ተናግረዋል።
ሥልጠናው የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ችግሮችን የሚፈታ ነው ያሉት ሠልጣኞቹ ሃብት በመፍጠርና ማሥተዳደር፣ የወል ገዢ ትርክት በመገንባት እና ሰላምና መልካም አሥተዳደርን ማስፈን በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንደሚደረግም ተገልጿል።
የሕዝቡ የአገልግሎት፣ የመልካም አሥተዳደር እና የሰላምና ጸጥታ ችግሮችን በመፍታት ረገድ ግልጽ ግንዛቤና አረዳድ ይዘው ወደ ሥራ ለመግባት እንደሚያግዝም ሠልጣኞች ተናግረዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!