
ባሕርዳር: ታኅሳሥ 12/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በሳኡዲ አረቢያ እየተደረገ በሚገኘው የዓለም የክለቦች ዋንጫ ዛሬ የፍጻሜና የደረጃ ጨዋታዎች ይከናወናሉ።በግማሽ ፍጻሜ የእንግሊዙ ማንቸስተር ሲቲ የጃፓኑን ኡርዋ ሬድስ፣የብራዚሉ ፍሉሚንዜ የግብጹን አል አህሊ አሸንፈው ለፍጻሜ ደርሰዋል።
ዛሬ ፍጻሜውን የሚያገኘው የዓለም የክለቦች ዋንጫ ማንቸስተር ሲቲን ከፍሉሚንዜ ለዋንጫ ያገናኛል። አል አህሊና ኡርዋ ሬድስ ደግሞ ለደረጃ ይጫወታሉ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!