
ባሕር ዳር: ታኅሳስ 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የበኩር ጋዜጣ 29 ዓመት የምስረታ በዓል እየተከበረ ነው። ጋዜጣዋ ታኅሣሥ 7/1987 ዓ.ም ነበር የተመሠረተችው።
በበዓሉ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉት የበኩር ጋዜጣ ዋና ዳይሬክተር ስንቅነሽ አያሌው “በኩር ብዙ ምቹ ባልኾነ ጊዜ ተመሥርታ ለሕዝብ አማራጭ የመረጃ ምንጭ መኾን የቻለች ጋዜጣ ናት” ብለዋል።
በኩር ቴክኖሎጂው ባለዘመነበት እና ብዙም የመረጃ ምንጭ አማራጮች ባልነበሩበት ጊዜያት ሁነኛ የመረጃ ምንጭ ነበረች ብለዋል። በውስን የሰው ኃይል የመንግሥትን አዋጆች፣ ማስታወቂያዎች እና ዘገባዎችን ለሕዝብ በማድረስ በኩል በክልል ደረጃ ቀዳሚ መኾኗንም አስረድተዋል።
አሚኮ የዘገባ ጥራቱን ጠብቆ ለሕዝብ ለመድረስ በሚያደርገው የማሻሻያ ሥራ መሠረት ጋዜጣዋ ከጥር/2016 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ ቅርጽ እና ይዘት ለአንባቢዎች እንደምትደርስ ዋና አዘጋጇ ጠቁመዋል።
ዘጋቢ፦ ሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!