
ባሕር ዳር: ታኅሳሥ 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የክልሉ መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተከትሎ 72 ታጣቂዎች ወደ መቀበያ ማዕከላት መግባታቸውን የወገራ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ ይናገር ወረታው ገልጸዋል።
በወረዳው ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት ከሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከሀገር ሽማግሌዎችና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ እየተሠራ እንደሚገኝም ዋና አሥተዳዳሪው ተናግረዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!