
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 09/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ሸዋ ዞን የግብዓት አቅርቦት ችግር እንዳያጋጥም እየሠራ መኾኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታውቋል፡፡ በ2015/16 የመኸር እርሻ ወቅት በሰው ሠራሽ እና ተፈጥሮአዊ ችግሮች ምክንያት የተጠበቀውን ያህል ምርት ማግኘት እንዳልተቻለም መምሪያው ገልጿል።
በተያዘው ዓመት ችግሮች እንዳያጋጥሙ 208 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በተለያዩ ዩኔኖች መግባቱን የመምሪያው ኀላፊ አቶ ታደሰ ማሙሻ ተናግረዋል።
ቀሪው 800 ሺህ ኩንታል ሰው ሠራሽ ማዳበሪያ በቅርቡ ወደ ዞኑ መጋዘኖች እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡
ምርትን ለማሳደግ የግብዓት አቅርቦት ወሳኝ እንደኾነ ያነሱት ኀላፊው አጠቃቀምን ከብክነት ማስተካከል እንደሚገባም መክረዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ገንዘብ ታደሰ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!