ፀደይ ባንክ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎትን አስጀመረ።

97

አዲስ አበባ: ታኅሳሥ 10/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ባንኩ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ማስጀመሩን አስመልክቶ መግለጫ ሠጥቷል።

የባንኩ ዋና ሥራ አስፋጻሚ መኮንን የለዉምወሰን ፀደይ ባንክ አሁን ካሉ ባንኮች ጋር ተፎካክሮ ማሸነፍ ግብ አድርጎ እየሠራ ነዉ ብለዋል።

ለዚህ መሰረቱ ቴክኖሎጅ አንዱ መኾኑን ያነሱት ዋና ሥራ አስፈጻሚዉ ባንኩን በቴክኖሎጂ ለማዘመን እየተሠራ ነዉ ብለዋል፡፡

ባንኩ የዚህ አካል የኾነዉን የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት አስጀምሯል ነው ያሉት።

የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎቱ ከምስጢር ቁጥር በተጨማሪ በአሻራ አገልግሎት መሥጠት እንዲችል ተደርጓል ነው ያሉት፡፡

አቶ መኮንን ከሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት በተጨማሪ ባንኩ የኮር ባንኪንግ አገልግሎትም መጀመሩን ገልጸዋል።

ባንኩ አጠቃላይ ካፒታሉ 12 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ደርሷል ተብሏል። አጠቃላይ ሃብቱ 55 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ማለፉንም ባንኩ አስታዉቋል።

ባንኩ እስከ ኅዳር 30/2016 ዓ.ም ድረስ የባንክ ቅርጫፎቹን ወደ 579 ማድረሱም ተገልጿል።

ከመስከረም 14/2015 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ ባንክ ኾኖ መመስረቱ ይታወሳል።

ዘጋቢ፡- ኤልሳ ጉኡሽ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበደብረ ማርቆስ ከተማ የተጀመሩ የመሠረተ ልማት ሥራዎች፦
Next articleከ333 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ለመሸፈን እየተሠራ መኾኑን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ገለጸ።