
ታኅሳሥ 10/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ሄሪልንግ ብራውንት ሐላንድ የቢቢሲ የዓመቱ ምርጥ ስፖርት ሽልማትን አሸነፈ፡፡
ማንችስተር ሲቲ በታሪኩ በአንድ የውድድር ዓመት ሦስት ዋንጫን እንዲያነሳ በማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽዖ የነበረው ግብ አዳኙ የቢቢሲ የዓመቱ ምርጥ ኮኮብ ተብሎ ተመርጧል፡፡
የ23 ዓመቱ አጥቂ ማንችሰተር ሲቲ በ2022/2023 የውድድር ዘመን የፕሪሚዬር ሊጉን፣ የኤፍካፑን እና የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግን ዋንጫ እንዲያነሳ ከፍ ያለ አበርክቶ ነበረው፡፡
በ2022/23 የውድድር ዘመን በሁሉም ውድድሮች 52 ግቦችን አስቆጥሯል፡፡ ከቦርሲያ ዶርትሙንድ ማንቸስተር ሲቲ እንደደረሰ የመጀመሪያ ዓመት ክብረ ወሰኖችን መሰባበር የጀመረው ሐላንድ በእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ በአንድ የውድድር ዘመን በርካታ ግቦችን የማስቆጠር ክብረ ወሰንን ሰብሯል፡፡
ሐላንድ በእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ በ38 ጨዋታዎች 36 ግቦችን በማስቆጠር በሞሐመድ ሳላህ ተይዞ የነበረውን በአንድ የውድድር ዘመን ከፍተኛ ግብ የማስቆጠር ክብረ ወሰን የግሉ አድርጓል፡፡
ተጫዋቹ“የዓመቱ ኮኮብ ተብዬ ስለተመረጥኩ አመሠግናለሁ፤ የአለፈው የውድድር ዘመን አስደናቂ ነበር፡፡ ሦስትዮሽ ዋንጫን አሸንፊያለሁ፣ አስደናቂ ነገር አድርገናል” ማለቱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በሴቶች ደግሞ የእንግሊዝ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ሜሪ ኢርፕስ የዓመቱ ምርጥ ተብላ ተመርጣለች፡፡
የ30 ዓመቷ ግብ ጠባቂ እንግሊዝ በዓለም ዋንጫ ፍጻሜ እንድትደርስ ካደረጉ ቁልፍ ተጫዋቾች መካከል አንደኛዋ ናት፡፡
በሴቶች የዓለም ዋንጫም የወርቅ ጓንት አሸናፊ መኾኗን ቢቢሲ አውስቷል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!