
ባሕር ዳር: ታኅሳሥ 10/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ዋና ተዳራዳሪው አምባሳደር ስለሽ በሰጡት መግለጫ የህዳሴ ግድብ ድርድር ባለፈው የኢትዮጵያ ግብፅ መሪዎች በተስማሙበት መሰረት ለ4ተኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ተካሒዶ ያለስምምነት መጠናቀቁን ጠቅሰዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለአካባቢው ዋነኛ የውኃ ቋት መኾኑን መገንዘብ ያስፈልጋል ነው ያሉት።
የህዳሴ ግድብ ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በድርቅ ጊዜ በሚኖር የውኃ አያያዝ እና አለቃቅ ላይ መሰረት ያደረገ ድርድር መደረጉን ያነሱት አምባሳደር ስለሽ በድርድሩ መርሆች ስምምምነት አንቀፅ 6 ላይ ግብፆች በውኃ ድርሻ ክፍፍል ላይ መደራደር ባለመፈለጋቸው ድርድሩ ያለስምምነት ተቋጭቷል ብለዋል።
በአንዱዓለም መናን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!