በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ የመንግሥትን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ 78 ታጣቂዎች በምህረት መግባታቸውን የወረዳው አሥተዳደር አስታወቀ።

107

ጎንደር: ታኅሣሥ 09/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በምህረቱ የገቡት ታጣቂዎች፣ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አመራሮች፣ የመከላከያ ሠራዊት አባላት እና የወረዳው አሥተዳደር በሰላም እና በቀጣይ ሥራዎች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

የዞኑ የሰላም እና ደኅንነት መምሪያ ኀላፊ ብርሃኑ ተድላ የሰላምን አማራጭ መርጣችሁ በመምጣታችሁ ተረጋግታችሁ ሕይዎታችሁን መምራት ትችላላችሁ ሲሉ በምህረት ለገቡት ግለሰቦች ገለጻ አድርገዋል።

ኀላፊው በዞኑ 507 ታጣቂዎች በምህረት መግባታቸውን ጠቅሰው 127 የተሃድሶ ሥልጠና መውሰዳቸውን ተናግረዋል።በሀገር መከላከያ ሠራዊት የ66ኛ ክፍለ ጦር ድጋፍ ሰጭ አገልግሎት ኀላፊ ኮሎኔል አዛናው ነጋሽ “ከሕዝቡ ጋር ባደረግናቸው ተደጋጋሚ ውይይቶች ታጣቂዎች በሰላም እየተመለሱ ነው” ብለዋል።

የምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ አሥተዳዳሪ ያለምሰላም ጌጡ ዛሬ ብቻ 78 ታጣቂዎች በሰላም የምህረቱ ተጠቃሚ መኾናቸውን ገልጸዋል። በምህረቱ የገቡት ታጣቂዎች በሰላማዊ መንገድ የሕዝብ ጥያቄዎች እንዲፈቱ ለመነጋገር የሰላም ጥሪውን ተቀብለው መግባታቸውን ጠቅሰዋል። ለራሳቸው እና ለአካባቢያቸው ልማት እንደሚሠሩም ጠቁመዋል።

ዘጋቢ፡- አገኘው አበባው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ኢትዮጵያ ከስፔን ጋር ያላትን ትብብር ወደ ስትራቴጂካዊ ደረጃ ለማሳደግ ፍላጎት አላት” አቶ ደመቀ መኮንን
Next article“አልሚዎች በገቡት ውል መሠረት ወደ ምርት እና የሥራ አድል ፈጠራ መግባታቸው አበረታች ነው” የደሴ ከተማ አሥተዳደር