ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በቴክኖሎጂ የታገዘ የንግድና ኢኮኖሚ ትስስር ሊኖራቸው እንደሚገባ ተገለጸ።

39

አዲስ አበባ: ታኅሳሥ 09/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ሚኒስቴር ከሩሲያ መንግሥት ተወካዮች፣ ባለሃብቶች እና የሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ነው።

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶ.ር) ኢትዮጵያ እና ሩሲያ ግንኙነታቸውን የሚመጥን በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ የንግድና ኢኮኖሚ ትስስር ሊኖራቸው እንደሚገባ ገልጸዋል።

የሩሲያ መንግሥት ኢትዮጵያን በአፍሪካ የባዮሎጂካል ጥናትና ምርምር መዳረሻ ለማድረግ እንደሚሠራም ተወካዮች ገልጸዋል።

ዘጋቢ:- ቤተልሄም ሰለሞን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሀገራዊ ምክክሩን ውጤታማ ለማድረግ የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮ መቃኘት ያስፈልጋል” የፖለቲካል ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ጥናት መምህር
Next articleለባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ ማጠናቀቂያ ከ970 ሚሊዮን ብር በላይ መፈቀዱ ተገለጸ።