ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ኢትዮጵያ ፍልሰተን ለመከላከል እና ከስደት ተመላሾችን መልሶ ለማቋቋም የምታደርገውን ጥረት እንደሚደግፍ አስታወቀ።

43

ባሕር ዳር: ታኅሳስ 9/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ኢትዮጵያ ፍልሰተን ለመከላከል እና ከስደት ተመላሾችን መልሶ ለማቋቋም የምታደርገውን ጥረት እንደሚደግፍ አስታውቋል።

የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ድኤታ ሁሪያ አሊ ከዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት የኢትዮጵያ ቺፍ ኦፍ ሚሽን አቢባቶው ዋኔ ጋር በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

ውይይታቸው መደበኛ ያልኾነ ፍልሰተን ለመከላከል፣ ከስደት ተመላሾችን መልሶ ለማቋቋም እና ተጋላጭ የሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው።
የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ድኤታ ሁሪያ አሊ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰተን ለመከላከል እና ከስደት ተመላሾችን መልሶ ለማቋቋም መንግሥት በልዩ ትኩረት እየሰራ መኾኑን ተናግረዋል።

የሴትችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ተጋላጭ የኾኑ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ የተለያዩ ፕሮግራሞችን በመቅረፅ ወደ ሥራ መገባቱን የተናገሩት ሚኒስትር ድኤታዋ ይህንን እንቅስቃሴ ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት እንዲደግፍ ጠይቀዋል።

የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት የኢትዮጵያ ቺፍ ኦፍ ሚሽን አቢባቶው ዋኔ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰተን ለመከላከል እና ከስደት ተመላሾችን መልሶ ለማቋቋም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።

መደበኛ ያልኾነ ፍልሰት መንስኤዎችን ለመለየት የሚያስችል ጥናት ለማካሄድ የገንዘብ፣ የቁሳቁስ እና የቴክኒክ ሃብቶች ውስንነቶችን መቅረፍ በሚቻልበት ዙሪያም መክረዋል።

የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንደገለጸው ሚኒስቴሩ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች ብሎ በለያቸው እና ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራትም ተስማምተዋል ተብሏል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበአማራ ክልል በድርቅ ለተጎዱ እና ለተፈናቀሉ ወገኖች የ10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገ።
Next articleወይዘሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ኾነው ተሾሙ።