ከ40 በላይ የቻይና አምራች ኩባንያዎች የተሳተፉበት የኢንቨስትመንት ፎረም ተካሄደ።

43

ባሕር ዳር: ታኅሳሥ 08/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ከ40 በላይ የቻይና አምራች ኩባንያዎች የተሳተፉበት የኢንቨስትመንት ፎረም በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

ፎረሙ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ – ቻይና የወዳጅነት እና ትብብር ኮሚቴ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ መሆኑ ተመላክቷል።

በፎረሙ ከቻይና ከጂሊን ግዛት እና ፉያንግ አሥተዳደር በኢትዮጵያ ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ የመጣ ከ40 በላይ ኩባንያዎች ተሳትፈውበታል።

ለኩባንያዎቹ በኢትዮጵያ ያሉ ዘርፈ ብዙ የኢንቨስትመንት ዕድል እና አማራጮች በተለይም በአምራች፣ በግብርና እና በማዕድን ዘርፎች ዙሪያ ዝርዝር ማብራሪያ እና ገለፃ ተደርጓል፡፡

የኩባንያዎቹ የልዑክ ቡድን በጂን ግዛት ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ጸሐፊ ፋን ራይፒንግ፣ የፉያንግ አሥተዳደር ምክትል ሴክረታሪ ጄኔራል ዋንግ ፈሂሁ እንዲሁም የኢትዮጵያ ቻይና የወዳጅነት እና ትብብር ኮሚቴ ሊቀ-መንበር ቤቲ ዡ ተመርቷል፡፡

ቡድኑ በቀጣይ ቀናት የተለያዩ አምራች ኩባንያዎችን የሚጎበኝ እና የኢንቨስትመንት አካባቢዎችን አንደሚቃኝ ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ወደ ስህተት የሚመራንን የሀሰት ወሬ አንሰማም፤ የሰላም ጀግኖች ኾነን ሕዝባችንን እንክሳለን” የሸዋ ሮቢት ማዕከል የተሃድሶ ሠልጣኞች
Next articleበአማራ ክልል በድርቅ ለተጎዱ እና ለተፈናቀሉ ወገኖች የ10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገ።