የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል፡፡

36

ባሕር ዳር: ታኅሳስ 8/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ ታኅሣሥ 9/2016 ዓ.ም በሚያካሄደው 9ኛ መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ሹመቶችን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ በሚያካሄደው 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ስብሰባው ነው የተለያዩ ሹመቶችን መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ የሚጠበቀው፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማኀበራዊ ትስስር ገጹ እንደገለጸው ምክር ቤቱ በ9ኛ መደበኛ ስብሰባው በቅድሚያ የ8ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤን በማጽደቅ የዕለቱን ስብሰባ ይጀምራል፡፡

ጉባዔው በዕለቱ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እጩ ሰብሳቢ ሹመትን መርምሮ እንደሚጸድቅም ይጠበቃል፡፡ ምክር ቤቱ በመደበኛ ጉባኤው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሹመትን እንደሚያፀድቅም ይጠበቃል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ድልድል ይፋ ኾነ፡፡
Next article“ወደ ስህተት የሚመራንን የሀሰት ወሬ አንሰማም፤ የሰላም ጀግኖች ኾነን ሕዝባችንን እንክሳለን” የሸዋ ሮቢት ማዕከል የተሃድሶ ሠልጣኞች