የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ድልድል ይፋ ኾነ፡፡

74

ባሕር ዳር: ታኅሳስ 8/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ድልድል ይፋ ሆኗል፡፡ 16 ቡድኖችን የሚያፎካክረው የሻምፒየንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ እጣ ማውጣት ተከናውኗል፡፡

በጥሎ ማለፉ የፖርቱጋሉ ኤፍሲ ፖርቶ ከእንግሊዙ አርሰናል፤ የዴንማርኩ ኤፍ.ሲ ኮፐንሃገን ከ እንግሊዙ ማንቸስተር ሲቲ፤ የጣልያኑ ናፖሊ ከስፔኑ ባርሴሎና፤ የፈረንሳዩ ፒኤስጂ ከስፔኑ ሪያል ሶሲዳድ ተደልድለዋል፡፡

የጣልያኑ ኢንተር ሚላን ከስፔኑ አትሌቲኮ ማድሪድ፤ የኔዘርላንዱ ፒኤስቪ አይንድሆቨን ከጀርመኑ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ፤ የጣልያኑ ላዚዮ ከጀርመኑ ባየር ሙኒክ፤ የጀርመኑ አርቢ ላይፕዚግ ከስፔኑ ሪያል ማድሪድ የተመደቡ ቡድኖች ናቸው፡፡

ዘጋቢ፦ ሙሉጌታ ሙጨ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የምድብ ድልድል ይፋ ኾነ፡፡
Next articleየሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል፡፡