
ታኅሳሥ 07/2016 ዓ.ም (አሚኮ)16 ቡድኖችን የሚያፎካክረው የሻምፒየንስ ሊግ የመጨረሻው የምድብ ድልድል ይፋ ኾነ፡፡
የፖርቱጋሉ ኤፍሲ ፖርቶ ከእንግሊዙ አርሰናል ፤የዴንማርኩ ኤፍ.ሲ ኮፐንሃገን ከ እንግሊዙ ማንቸስተር ሲቲ ፤ የጣልያኑ ናፖሊ ከስፔኑ ባርሴሎና ፤ የፈረንሳዩ ፒኤስጂ ከ ስፔኑ ሪያል ሶሲዳድ ተደልድለዋል፡፡
የጣልያኑ ኢንተር ሚላን ከስፔኑ አትሌቲኮ ማድሪድ፤ የኔዘርላንዱ ፒኤስቪ አይንድሆቨን ከጀርመኑ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ፤ የጣልያኑ ላዚዮ ከጀርመኑ ባየር ሙኒክ፤ የጀርመኑ አርቢ ላይፕዚግ ከስፔኑ ሪያል ማድሪድ ተደልድለዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!