
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 08/2016 ዓ.ም (አሚኮ) 4ኛው ዙር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡
የኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን የሶስትዮሽ ድርድር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እና ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አል-ሲሲ በሐምሌ ወር መጀመሪያ ተገናኝተው የሰጡትን የጋራ መግለጫ ተከትሎ እየተካሄደ ያለ ነው።
ድርድሩ በህዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌትና አለቃቀቅ ደንቦችና መመሪያዎች ላይ ስምምነት ለመድረስ ያለመ መሆኑን የኢትዮጵያ ወገን ተደራዳሪዎች ልዑካን መሪ አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ.ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡ ባለፉት ዙሮች በተደረጉ ድርድሮች እና የተለያዩ ጉዳዮች ላይ የተሻለ መግባባት ላይ ለመድረስ ትኩረት እንደሚደረግም አንስተዋል፡፡
ኢትዮጵያ በ2015 በመሪዎች ደረጃ የተፈረመው የመርሆች መግለጫ ስምምነት መሰረት ድርድሩን በፍትሃዊና ምክንያታዊ አጠቃቀም መርህ መሰረት ውጤት ላይ ለመድረስ እንደምትሠራ አስገንዝበዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!