በኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን መካከል 4ኛው ዙር የሦስትዮሽ ድርድር ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀመረ።

52

ባሕር ዳር: ታኅሳሥ 08/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የሦስትዮሽ ድርድሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እና ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አል-ሲሲ ባለፈው ሐምሌ ወር መጀመሪያ አካባቢ ተገናኝተው የሰጡትን የጋራ መግለጫ ተከትሎ እየተካሄደ ያለ ነው ተብሏል፡፡

የሁለቱ ሀገራት መሪዎች የሦስቱ ሀገራት ተወካዮች ድርድሩን በማፋጠን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር ሙሌት እና ቀጣይ ተግባራትን የተመለከቱ መመሪያዎች እና ደንቦችን እንዲያዘጋጁ ከመግባባት ደርሰው እንደነበር ይታወሳል፡፡

በሚኒስትሮች ደረጃ እየተካሄደ ያለው ድርድር ዓላማው ቀደም ሲል የተካሄዱ ውይይቶችን በማዳበር ከጋራ መግባባት ላይ መድረስ እንደኾነ አምባሳደር ዶክተር ኢንጅነር ስለሽ በቀለ በማኅበራዊ ገጻቸው ጠቁመዋል፡፡

በድርድሩ ኢትዮጵያ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2015 የተደረሰበትን የመርሆ ሥምምነት መሠረት አድርጋ እየተሳተፈች እንደኾነም ተጠቁሟል፡፡ ኢትዮጵያ ፍትሃዊ እና ምክንያታዊ የውኃ አጠቃቀም ላይ የተመሰረተ ሥምምነት እንዲኖር ጥረት ማድረጓን ትቀጥላለችም ተብሏል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሩሲያ ባለሃብቶች በአምራች ኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት ዘርፍ እንዲሳተፉ ተጠየቀ።
Next article“ባለፉት አምስት ወራት ከ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በወባ በሽታ ተይዘዋል” ጤና ሚኒስቴር