ኢትዮጵያ አየር ኃይል እጩ መኮንኖችን፣ ቴክኒሻኖችንና አብራሪዎችን አስመረቀ።

50

ባሕር ዳር: ታኅሳሥ 06/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የኢትዮጵያ አየር ኃይል በ88ኛው ዓመት የምስረታ በዓሉ እጩ መኮንኖችን፣ ቴክኒሻኖችንና አብራሪዎችን አስመርቋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ ከ5 ዓመት በፊት በየጫካው ተጥለው የነበሩ አውሮፕላኖችን አንስተን የዘመኑ ቴክኖሎጂ በመግጠም ወደ ዝግጁነት መመለስ ችለናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል በአሁኑ ወቅት የራሱን የሠው ኃይል ከማብቃት አልፎ ለሌሎች አፍሪካ ሀገራት ሙያተኞችን በማሰልጠን ድጋፍ እንደሚያደርግም ገልፀዋል።

አየር ኃይሉ የእውቀት እና የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማረጋገጥ በርካታ ስራዎችን ሠርቷል ያሉት ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ በዛሬው ዕለት ተተኪ መኮንኖችን፣ አብራሪዎችንና የአውሮፕላን ጥገና ሙያተኞችን አሰልጥነን አብቅተናል ብለዋል።

በሠው ኃይል፣ በትጥቅ እና በመሠረተ ልማት የገነባነው አቅም የውስጥ እና የውጭ ጠላቶች ደጋግመው እንዲያስቡ የሚያደርግ ነውም ነው ገለጹት።

የኢትዮጵያ አየር ሃይል 88ኛ ዓመት የምስረታ በዓል የማጠቃለያ ፕሮግራም እየተካሄደ ይገኛል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“አየር ኀይል ለሀገር ሉዓላዊነት እና አንድነት በተለያዬ ጊዜ ወርቃማ ገድሎችን ፈጽሟል” ሌትናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ
Next article“ከዓለም አቀፍ የኃይል አሰላለፍ እና ከዘመኑ የውጊያ አውድ አኳያ ኢትዮጵያ አየር ኃይሏን እንደምታዘምን ይታወቃል” ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ