
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 06/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ሰላምን ለማረጋገጥ ከልብ የመነጨ እርቅ እና ይቅርታ ማድረግ እንደሚገባ የአማራ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አሳስቧል።
ባለፉት ዓመታት በክልሉ በተፈጠረው ችግር በምዕመኑ ላይ የሕይዎት መጥፋት እና የንብረት ውድመት መድረሱን የጉባዔው አባላት ገልጸዋል።
ሃይማኖታዊ ተግባራትን ለመከወንም ፈተና ኾኖ እንደቆየ ተገልጿል።
የጋራ ሀገር ለመገንባት ጥላቻን ማስወገድ ተቀዳሚ ተግባር ሊኾን እንደሚገባ የጉባዔው አባላት አንስተዋል።
ለዚህ ደግሞ ሁሉም በየሃይማኖቱ ፈጣሪን በጾሎት መለመን ይገባል ነው ያሉት።
ከዚህም ባለፈ ከልብ የመነጨ እርቅ እና ይቅርታ እንዲደረግም ጠይቀዋል።
መንግሥት ከሰላም ጥሪው ባለፈ በቀጣይም በሕዝብ የሚነሱ ጥያቄዎችን በሆደ ሰፊነት እንዲፈታም ተጠይቋል።
በተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት ሥር የሚገኙ ምዕመናንም ስለ ሰላም እንዲሠሩ አሳስበዋል።
ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሠራ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!