“በኢትዮጵያና በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች አየር ኃይሎች በጋራ የቀረበው ወታደራዊ የአየር ላይ ትርዒት በትብብር ከሠራን የምንደርስበትን ደረጃ ያሳየ ነው።” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

50

ባሕር ዳር: ታኅሳሥ 06/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ የኢትዮጵያ አየር ኃይል የተመሠረተበትን 88ኛ በዓል በቢሾፍቱ ሐረር ሜዳ ግቢ አክብረናል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት መሠረተ ልማትና ዘመናዊ ትጥቆችን ለማሟላት፤ ራስን በቴክኖሎጂ ለመቻል፣ ብቁና በቂ የሰው ኃይል ለማፍራት፤ የተደረገው ጥረት ሪፎርማችን ውጤታማ መሆኑን አሳይቷል።

በበዓሉ ላይ በኢትዮጵያና በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች አየር ኃይሎች በጋራ የቀረበው ወታደራዊ የአየር ላይ ትርዒት በትብብር ከሠራን የምንደርስበትን ደረጃ ያሳየ ነው። በሁሉም ዘርፍ ኢትዮጵያን ወደ ብልጽግና መምራታችንን እንቀጥላለን ብለውል በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልእክት።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበየአካባቢያቸው ታጥቀው የወጡ አካላት ለሰላም ጥሪዉ ተገዥ እንዲኾኑ እንደሚሠሩ የሃይማኖት አባቶች ገለጹ፡፡
Next article“ጥቁር አንበሳ የአየር ትርኢት ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች በጋራ ለመሥራት ያላቸውን ጽኑ ፍላጎት በግልጽ ያሳየ ነው” ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ