“የኢፌዴሪ አየር ኃይል ከዚህ በፊት ከነበረበት የፖለቲካ ውግንና በመላቀቅ ጠንካራ ተቋም ማድረግ ችለናል” ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ

20

አዲስ አበባ: ታኅሳስ 5/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የኢፌዴሪ ጦር ኀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የኢፌዴሪ አየር ኃይል ተቋማዊ አቅም እና ሂደትን አስመልከቶ በተዘጋጀ መድረክ ላይ “አየር ኃይሉን ከዚህ በፊት ከነበረበት የፖለቲካ ውግንና ነፃ በማድረግ ጠንካራ ተቋም ማድረግ ተችሏል” ብለዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ከዚህ በፊት ለአየር ኃይሉ አንዱ የተሻለ የሚያሰብ ሌላው ደግሞ ተቆርቋሪ ያልኾነ ተድርጎ ይሳል ነበር ብለዋል። አሁን ግን ሁሉም ለተቋሙ የሚያስብ ከፖለቲካ አባልነት የፀዳ ማድረግ መቻሉንም አስረድተዋል።

አየር ኃይሉ ከዚህ በኋላ በምንም ዓይነት መንገድ የማይፈርስ እና የማይንገዳገድ ተቋም ተደርጎ እየተሠራ እንደሚገኝም ነው ያስገነዘቡት።

የአየር ኃይል 88ኛ ዓመቱ ሲከበር አየር ኃይሉ የሀገር አቅም መኾኑን ለማሳየት ታሳቢ ያደረገ እንደኾነ ተገልጿል፡፡

በዓሉም ጀግኖች መስዋት እየከፈሉ በቅብሎሽ ያመጡት መኾኑን ለማሳወቅ የሚያስችል ነው ብለዋል።

ዘጋቢ፡- አንዱዓለም መናን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleትኩረት ያገኙ የስምንተኛ ሳምንት መርኃ ግብሮች ዛሬ ይካሄዳሉ።
Next article“ሁሉም ለሰላም ይቁም” የሃይማኖት አባቶች