የዓድዋ ዜሮዜሮ ፕሮጀክት የደረሰበትን የግንባታ ሂደት የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር አስጎበኘ።

41

አዲስ አበባ: ታኅሳሥ 05/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የከተማ አሥተዳደሩ ቢሮ ኀላፊ ጥላሁን ከበደ ከተማ አሥተዳደሩ ከያዛቸው ትልልቅ ፕሮጀክቶች አንዱ የዓድዋ ዜሮዜሮ ፕሮጀክት እንደኾነ ገልጸዋል፡፡

ፕሮጀክቱ የዓድዋ ታሪክን በመዘከር የኢትዮጵያን ገጽታ ከመገንባት ባለፈ ለአፍሪካም ጭምር የአሸናፊነትን ታሪክ የሚያጎናጽፍ እንደኾነ አስረድተዋል። ፕሮጀክቱ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል ያሉት ኀላፊው የተወሰኑ ሥራዎች ብቻ የቀረው መኾኑን አንስተዋል።

ፓን አፍሪካኒዝምን የሚዘክር የፕሮጀክቱ አካል የኾነ አዲስ ግንባታ ተጀምሮ እየተሠራ መኾኑንም አቶ ጥላሁን ጠቅሰዋል ። የዓድዋ ዜሮዜሮ ፕሮጀክት ሙዚየም የተለያዩ በሀገሪቱ የታሪክ ሰንሰለት የነበሩ ታሪኮችን የያዘ በተለይም የዓድዋን ታሪክ ለትውልድ ለማስተላለፍ ታስቦ እየተገነባ መኾኑም ተመላክቷል።

ከተማ አሥተዳደሩ የፕሮጀክቱን የግንባታ ሁኔታ እና ያለበትን የግንባታ ደረጃ ለመገናኛ ብዙኃን እና ለተለያዩ ባለድርሻ አካላት አስጎብኝቷል። የዓድዋ ድል የተበሰረበት ነጋሪት በተንጣለለው የሙዚየሙ ስፍራ የተቀመጠ ሲኾን በሙዚየሙ የአጼ ምኒልክ እና እቴጌ ጣይቱን የሚዘክር ሀውልት የሚቀመጥ እንደኾነ ተገልጿል። ሙዚየሙ በዓድዋ ታሪክ ዋጋ የከፈሉ ኢትዮጵያዊያን የሚዘክሩ የቅርስ ማሰባሰብ ሥራዎች እንደሚቀጥሉ ተመላክቷል።

ዘጋቢ፡- አየለ መስፍን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየመንግሥት ሠራተኞች ከአሉባልታ ወሬ በመራቅ ለሰላሙ ጥሪ ዘብ ሊቆሙ እንደሚገባ የሰቆጣ ከተማ አሥተዳደር የመንግሥት ሠራተኞች ጠየቁ።
Next article“የክልሉ መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ በመስማታችን ስጋታችን ወደ ተስፋ ተቀይሯል” የጣና ፍሎራ ሠራተኛ