
ጎንደር: ታኅሳስ 3/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የቀረበው የሰላም ጥሪ ተቀራርቦ በመነጋገር በሰላማዊ መንገድ ችግሮችን ለመፍታት ያስችላልም ብለዋል አስተያየታቸውን ለአሚኮ ያጋሩ የከተማዋ ነዋሪዎች፡፡
ነዋሪዎቹ የሚነሱ ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ ለመመለስ እና ችግሮችን በወቅቱ ለመፍታት መንግሥት እና ሕዝብ በሆደ ሰፊነት መሥራት ይገባቸዋልም ብለዋል።
ለዚህም የሃይማኖት አባቶች፣ የሲቪክ ማኅበራት፣ የሀገር ሽማግሌዎችን ጨምሮ ማኅበረሰቡን በስፋት ያካተቱ ውይይቶችን ማካሄድ ይጠበቃል ብለዋል። ተቀራርቦ መነጋገር እና የጋራ ችግርን መፍታት አስፈላጊ እንደኾነም አንስተዋል። የሰላም ሚና ጉልህ ነው የሚሉት ነዋሪዎቹ ይህን በመገንዘብ ለሰላም ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባም አብራርተዋል።
ዘጋቢ፡- ቃልኪዳን ኃይሌ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!