በተዛባ መንገድ በተሰራጨ መረጃ ተገቢ ባልኾነ ግጭት ውስጥ መግባታቸውን የገለጹ 127 ዜጎች የተሀድሶ ሥልጠና ወስደው ወደ ማኅበረሰቡ ተቀላቀሉ።

34

ጎንደር: ታኅሳስ 3/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር የተሃድሶ ሥልጠና ማዕከል ሥልጠናቸውን ያጠናቀቁ 127 ዜጎች ወደ ማኅበረሰቡ ተቀላቀሉ።

ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን እና ከጎንደር ከተማ አሥተዳደር በጎንደር የተሀድሶ ሥልጠና ማዕከል ገብተው ሥልጠናቸውን ያጠናቀቁ 127 ዜጎች ወደማህበረሰቡ ተቀላቀሉ።

በየአካባቢያቸው በጸጥታ መደፍረስ ተሳትፈዋል ተብለው የተለዩ እና ወደ ሰላማዊ አማራጮች የተመለሱ ሠልጣኞች ሥልጠናቸውን አጠናቅቀዋል። የሕዝብን ጥያቄ ለማስመለስ የሄድንበት መንገድ የተሳሳተ ነበር ያሉት ሠልጣኞቹ ሰላማዊ ትግል መከተል የምንችልበትን አግባብ አይተናል ብለዋል።

ሠልጣኞቹ በሠላማዊ መንገድ በመታገል ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ እንዲያገኙ ከማኅበረሰቡ ጋር በጋራ እንደሚሠሩም አረጋግጠዋል።

የክልሉን ሕዝብ ጥያቄዎች ማስመለስ የሚቻለው ቅድሚያ ሰላም ሲሰፍን ነው ያሉት የጎንደር ተሃድሶ ሥልጠና ማዕከሉ አስተባባሪ አቶ አቤል መብት በሠልጣኞቹ የሚነሡ ጥያቄዎች በሚፈቱበት መንገድ ከስምምነት ላይ መደረሡን አብራርተዋል።

ሠልጣኞቹ በተዛባ መንገድ በተሰራጨው መረጃ ተገቢ ባልሆነ ግጭት ውስጥ መግባታቸውን የገለጹት ሠልጣኞቹ አሁን በድርጊታቸው መጸጸታቸውን ነው የ102ኛ ኮር ፍትሕ ቡድን አስተባባሪ ሻለቃ ከማል ገበያው ያስረዱት።

ሠልጣኞቹ በሥልጠና ቆይታቸው ወደ ማኅበረሰቡ ሲቀላቀሉ የየአካባቢያቸው የሰላም አምባሳደር መኾን እንዳለባቸው ግንዛቤ ያገኙበት እንደነበርም ሻለቃ ከማል ገልጸዋል።

ዘጋቢ፦ ተስፋዬ አይጠገብ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ምልክቱ ይህ ነው የንጉሥ ሞት ሀዘን ጣይቱ ስትጨልም ጨረቃ ደም ስትኾን”
Next articleወታደራዊ አታሼዎች የብላቴ የኮማንዶና አየር ወለድ ማሠልጠኛ ማዕከልን ጎበኙ።