
ባሕር ዳር፡ የካቲት 12/2012 ዓ.ም (አብመድ) የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አራት የመንገድ ፕሮጀክቶችን የውል ስምምነት ከተቋራጭ ድርጅቶች ጋር ዛሬ ተፈራርሟል፡፡
የጎንጂ-ቆለላ (ቆሬ-አዲስ አለም)፣ የግሸን መገንጠያ ዲዛይንና ግንባታ፣ የቆሼ-ሚጦ-ወራቤ እንዲሁም የጋምቤላ-አቦቦ-ዲማሎት የመንገድ ሥራ ፕሮጀክቶች ውል ነው የተፈረመው።
ኢ.ፕ.ድ እንደዘገበው በፊርማ ስነ ስርአቱ ላይ መንገዶቹ ከሚሰሩባቸው አካባቢዎች የተወከሉ የሀገር ሽማግሌዎችና የአስተዳደር አካላት ተገኝተዋል።