
አዲስ አበባ: ታኅሳሥ 03/2016 ዓ.ም (አሚኮ) 120 ድርጅቶችን ያሳተፈ “ኢትዮጵያ ታምርት፣ እኛም እንሸምት” የተሰኘ የአምራች ኢንተርፕራይዞች ኤግዚቢሽንና ባዛር በልዩ አቀራረብ በአዲስ አበባ ከተማ ዛሬ በይፋ ተከፍቷል።
በኢግዚቢሽን እና ባዛሩ የተለያዩ የቆዳና የጨርቃጨርቅ ምርቶች፣ ማሽነሪዎች፣ የአግሮ ፕሮሰሲንግ ውጤቶች፣ ኬሚካል፣ የኢንጂነሪንግ እና የቴክኖሎጂ ውጤቶች ይገኛሉ።
ባዛሩ እስከ ታኅሳሥ 7/2016 ዓ.ም ድረስ ለተሳታፊዎች፣ ለጎብኝዎች እና ለሸማቾች ክፍት እንደሚኾን ተገልጿል።
ዘጋቢ:- ቤቴል መኮንን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!