የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዎች ዛሬና ነገ ይካሄዳሉ።

31

ባሕር ዳር: ታኅሳሥ 02/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዎች ዛሬና ነገ ይካሄዳሉ። በምድብ አንድ በሻምፒዮንስ ሊጉ ለመቆየት አጣብቂኝ ውስጥ የሚገኘው ማንቸስተር ዩናይትድ ባየርሙኒክን ይገጥማል። ዩናይትድ በምድቡ አራት ነጥብ ይዞ የምድቡ ግርጌ ላይ ተቀምጧል። ባየርሙኒክ ደግሞ ጥሎ ማለፉን ተቀላቅሏል።

በዚሁ ምድብ ኮፐን ሃገን ከጋላታሳራይ የሚያደርጉት ጨዋታም የምድቡን ሁለተኛ አላፊ ቡድን ይለያል።ሁለቱ ክለቦች እኩል አምስት ነጥብ ይዘዋል።

ማንቸስተር ዩናይትድ ወደቀጣይ ዙር ለማለፍ ባየር ሙኒክን ማሸነፍ እና የኮፐን ሃገን እና የጋላታሳራይን ጨዋታ አቻ መጠናቀቅ ይጠብቃል።

ምድብ ሁለት ላይ አርሴናል ቀድሞ የምድብ ድልድሉን ተቀላቅሏል። ፒስቪ እና ሌንስ ሁለተኛ ኾነው የማጠናቀቅ እድል አላቸው።የስፔኑ ሲቪያ በምድቡ ግርጌ ላይ ይገኛል። ሌንስ ከሲቪያ፣ ፒስቪ ከአርሴናል ዛሬ የሚደረጉ የምድቡ ጨዋታዎች ናቸው።

ሪያል ማድሪድ እና ናፖሊ ጥሎ ማለፉን በተቀላቀሉበት ምድብ ሦስት ዩኔን በርሊን ከሪያል ማድሪድ፣ ናፖሊ ከስፖርቲንግ ይገናኛሉ።

በምድብ አራት ኢንተርሚላን ከሪያል ሶሴዳድ፣ አርቢ ሳልዝበርግ ከቤኔፊካ ይፋለማሉ። ሪያልሶሴዳድ እና ኢንተርሚላን 16ቱን መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል።

አስማማው አማረ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበምሥራቅ አማራ ያለውን ሰላም ለማጽናት ከሃይማኖት አባቶች እና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በኮምቦልቻ ከተማ ምክክር እየተካሄደ ነው፡፡
Next articleየአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በክልሉ ግጭት እንዲያበቃ እና አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን የሰላም ጥሪ አቀረበ።