በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የኾነው የአቪዬሽን ኢኖሼሽን ኤክስፖ ተከፈተ፡፡

64

ባሕር ዳር: ታኅሳሥ 01/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ኤክስፖው በዛሬው ዕለት “ፈጠራ ለአቪዬሽን ልህቀት ” በሚል መሪ ሃሳብ ነው በሳይንስ ሙዚየም የተከፈተው፡፡

በኤክስፖው ላይ የአቪዬሽን ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን የፈጠራ ውጤቶች፣ ምርቶችና አገልግሎቶች ቀርበዋል፡፡

ተከታታይ የአቪዬሽን ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ የውይይት መድረኮችም ይካሄዱበታል ተብሏል።

ኤክስፖው በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ባለቤትነት እንዲሁም በትራንስፖርት ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር አስተባባሪነትና ከሌሎች ተቋማት ጋር በመተባበር እንደተዘጋጀ ኤፍቢሲ አስነብቧል፡፡

በመክፈቻ መርሐ ግብሩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል ተመስገን ጥሩነህና የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በጦርነት የተጀመረ እንጂ በጦርነት የተቋጨ ችግር የለም” አቶ ደጀኔ ልመንህ
Next article“የዘንድሮውን የልደት በዓል በላሊበላ ከእስካሁኑ በተለየ መልኩ በልዩ ድምቀት ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ ነው” የላሊበላ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ወንድምነው ወዳጀ