“ኢትዮጵያዊያን በዜግነት ድርና ማግ ኾነን የምንኖር ሕዝቦች ነን” ሙስጠፋ ሙሐመድ

40

ባሕር ዳር: ኅዳር 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) 18ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል በሶማሊ ክልል ጅግጅጋ ከተማ እየተከበረ ነው፡፡

“ብዝኃነት እና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት” በሚል መሪ መልእክት በሚከበረው 18ኛው በዓል ክልሎች እና ከተማ አሥተዳደሮች በምሥራቃዊቷ ሶማሊ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ተሰባስበዋል፡፡

የ18ኛ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል አስተናጋጁ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሙስጠፋ ሙሐመድ በዓሉ አንድነታችን በማጠናከር ኅብረ ብሔራዊነታችን የምናጸናበት ነው ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያዊያን የተለያየ ባሕል፣ እምነት እና ማንነት ይዘው ሀገር ማጽናት እንደሚችሉ የቆየ ልምድ እና እሴት አላቸው ብለዋል፡፡

“እኛ ኢትዮጵያዊያን በዜግነት ድርና ማግ ኾነን የምንኖር ሕዝቦች ነን” ያሉት ርእሰ መሥተዳድር ሙስጠፋ ተፈጥሮ የሰጠችን ጸጋ እና ሃብት በአግባቡ አልምተን ለመጠቀም ወንድማማችነትን ማጽናት ይኖርብናል ብለዋል፡፡

ክልሉ ለሁለተኛ ጊዜ በዓሉን እንዲያዘጋጅ እድል ስለተሰጠውም እናመሰግናለን ብለዋል፡፡ ዝግጅቱ የክልሉን እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ማንነት ለማሳየት እድል የሰጠ ነበር ብለዋል፡፡

በታዘብ አራጋው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየብልጽግና ፓርቲ ለብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፈ።
Next article“ሀገር እንደ ሀገር ጸንታ እንድትቀጥል ሁላችንም የድርሻችንን መወጣት ብቻ በቂ ነው” አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር