የተለያዩ ሚስዮኖች 18ተኛውን የብሔር ፣ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል እያከበሩ ነው።

31

ባሕር ዳር: ኅዳር 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ብዝኀነት እና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት’’ በሚል ሀሳብ የሚከበረው 18ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሚስዮኖች በተለያዩ ሥነ ሥርዓቶች በመከበር ላይ ነው።

በዓሉን ካከበሩት መካከል በጅቡቲ፣ ካይሮ ፣ ቴል አቪቭ፣ ኢስላማባድ እንዲሁም ሪያድ ሚገኙት የኢትዮጵያ ሚስዮኖች ይገኙበታል።

በክበረ በዓሉ ላይ በየሚሴዮኖቹ ከሚገኙት ዲኘሎማቶች እና ሠራተኞች በተጨማሪ በየሀገራቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ተሳታፊ ሆነዋል።

የኢትዮጵያን ባሕል፣ ትውፊት እና ታሪክ የሚያስተዋውቁ ዝግጅቶችም በመርኃ ግብሮቹ ላይ መቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ቀምበር አሠቃይ፤ ዘር አሥነቃይ”
Next articleየብልጽግና ፓርቲ ለብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፈ።