“ኅብረ ብሔራዊነታችን ውበታችን መኾኑን በመገንዘብ ለመፃኢ እድላችን በጋራ መቆም ይገባናል” አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር

37

አዲስ አበባ: ኅዳር 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ) 18ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓልን በምታስተናግደው ጅግጅጋ የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች በሀገራዊ አጀንዳ እየመከሩ ነው።

ምክክሩ የዴሞክራሲ ባሕል ግንባታን መሰረት ለመጣል የሚያስችል እንደኾነም ተገልጿል፡፡

በምክክሩ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ የሁሉም የክልል ርእሳነ መሥተዳደሮች፣ የምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች፣ የከተማ ከንቲባዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ነው።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር እንዳሉት ኢትዮጵያዊያን የብዙ ባሕሎች፣ ታሪኮች እና ቅርሶች ባለቤት ናቸው።

አፈጉባዔው በዚህች ኅብረብሔራዊ በኾነች ሀገር የኔ ብቻ የሚል አስተሳሰብ መኖር እንደሌለበት አስገንዝበዋል።

አፈጉባኤ አገኘሁ “ኅብረብሔራዊነታችን ውበታችን መኾኑን በመገንዘብ ለመፃኢ እድላችን በጋራ መቆም ይገባናል” ብለዋል። በዓሉ ሀገራዊ አንድነትን እና ኅብረብሔራዊነትን ማሳያ እንደኾነም አብራርተዋል።

ዘጋቢ፦ አብነት እስከዚያ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ማዕከሉ ዋና መቀመጫውን በሀገራችን ማድረጉ ኢትዮጵያ ለጥቁር ሕዝቦች ነፃነት ላበረከተችው ጉልህ አስተዋጽኦ ዕውቅና የሚሰጥ ነው” አቶ ደመቀ መኮንን
Next articleየካናዳ ሐኪሞች እርዳታ እና ድጋፍ ማኅበር የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።